አዋሽ ባንክ ጃክሮስ ቅርንጫፍ ዝርፊያ ተፈጸመበት

“ዘራፊዎቹ አምስት ናቸው። መሳሪያ የታጠቁ እና በሞተር ሳይክል የመጡ ናቸው” ~ የባንኩ ተረኛ ጥበቃ ብርሃኑ ሁንዴ

“… ወንጀሉ ተፈጽሟል። በጣም ይቅርታ አሁን ዝርዝር መረጃ ልሰጥህ አልችልም!” ~ የቦሌ ወረዳ የ CMC ፖሊስ ጣቢያ መርማሪ ሚኪያስ ደረሰ

“ተጯጩኸን … በሕዝቡ ርብርብ አንዱን ሞተረኛ ይዘናል! …ሌሎቹ አምልጠውናል ” ~ የዓይን እማኝ

“አዎ የባንኩ ጥበቃ ነኝ። መሳሪያ የያዝኩት እኔ ነበርኩ። ሽጉጥ ደቅነው እኔንም ጓደኛዬን ወደ ውስጥ አስገቡን። ከዚያም ወደ ላይ ተኮሱ። በያዙት ቦርሳ መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ ዘርፈው አምልጠዋል። ጩኸት አሰማን። ከኅብረተሰቡ ጋር በመተባበር አንዱ ተይዟል” ~ የአዋሽ የባንኩ ተረኛ ጥበቃ ብርሃኑ ሁንዴ

 

You Might Be Interested In